BBC News, አማርኛ - ዜና

ዜና

ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ

አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ

የዓለም ዋንጫ - 2026

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች

አነጋጋሪ ጉዳይ

  • ባላለቁ ሕንጻዎቹ እና የሚውለበለብ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ

    የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚከስሱ ሲናገሩ የነበሩት የቦንድ አበዳሪዎች እንዴት ከስምምነት ደረሱ?

    ከአንድ ወር በፊት ለኢትዮጵያ ገንዘብ ያበደሩ ባለሀብቶች የአገሪቱን መንግሥት እንደሚከስሱ አስታውቀው ነበር። ትናንት ሰኞ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም. ግን የገንዘብ ሚኒስቴር ከባለሀብቶቹ ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መደረሱን አስታውቋል።

  • የኤርትራ ናቅፋ የሚቆጥር ሰው እጅ

    የኤርትራ መንግሥት ዜጎች በእጃቸው ያለ ገንዘብን በአንድ ወር ወደ ባንክ እንዲያስገቡ አዘዘ

    የኤርትራ መንግሥት ዜጎቹ በእጃቸው ላይ ያለ ገንዘብን በሙሉ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ወደ ባንክ እንዲያስገቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ አወጣ። የኤርትራ ማዕከላዊ ባንክ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ጥብቅ ማሳሰቢያ፤ በአገሪቱ ውስጥ በግለሰቦች እና በተቋማት እጅ የሚገኝ የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ (ናቅፋ) በሙሉ ዛሬ የጀመረው የአውሮፓውያን ሐምሌ ወር መጠናቀቂያ ድረስ ወደ ባንክ እንዲገባ አዝዟል።

  • በሆሳዕና ከተማ በተለያዩ ጊዜያት የውሾች ክትባት መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል

    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሆሳዕና ከተማ 400 ገደማ ውሾች ለምን እና እንዴት ተገደሉ?

    ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሾች በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳዩ ምሥሎች በማኅበራዊ ሚዲያ ከተጋሩ በኋላ በርካቶችን አስቆጥቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ነዋሪዎች እና የከተማዋ ባለሥልጣን እንዳሉት ውሾቹን በጅምላ መግደል የተጀመረው ሦስት ታዳጊዎች ከእብድ ውሻ በሽታ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ነው።

  • ማቀዝቀዣ ውስጥ ወተት የምታስቀምጥ የጤና ባለሙያ

    በኢትዮጵያ የተከፈተው የመጀመሪያው የእናት ጡት ወተት ባንክ የሚሰጠው አገልግሎት ምንድን ነው?

    በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነ የእናት ጡት ወተት ባንክ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ተከፈተ። ባንኩ ከለጋሽ እናቶች የተሰበሰበ ወተት የደኅንነት ሂደቶችን አልፎ የሚጠራቀምበት ሲሆን፣ ወተቱ በተለያየ ምክንያት ከእናቶቸቻው የጡት ወተት ማግኘት ለማይችሉ ጨቅላ ሕፃናት ያቀርባል።

  • የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

    የመንግሥት ቅርጽ፣ አንቀጽ 39 እና የአዲስ አበባ ጉዳይ በሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ውስጥ ተካተቱ

    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ሐምሌ ሊካሄድ ቀን በተቆረጠለት አገር አቀፍ ጉባኤ ለውይይት ይፋ የሚሆኑ ስምንት ዋነኛ አጀንዳዎችን ይፋ አደረገ። ኮሚሽኑ ይፋ ካደረጋቸው የምክክር አጀንዳዎች መካከል "የመንግሥት አደረጃጀት ሥርዓት ዓይነት" እና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 የተደነገገው "የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት" ጉዳዮች ተካትተዋል።

  • በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ

    አሜሪካ በትግራይ የሰላም ሂደትን "የሚያደናቅፉ አካላትን" አሳሰበች

    በትግራይ የሰላም ሂደትን "እያደናቀፉ ያሉ አካላት" ለውይይት ጥረቶች ትብብር እንዲያደርጉ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ማሳሰቢያ ሰጠ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የፖለቲካ እና የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች በፖለቲካ ውይይት ውስጥ መሳተፍ እና የፕሪቶሪያውን ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ መተግበር እንዳለባቸው አሳስቧል።

  • የትግራይ ኃይሎች

    የትግራይ ክልል ምክር ቤት የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን የያዘው አወዛጋቢ አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን አዘዘ

    ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ወደ ሥራ የመለሰው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን እና በሞት የሚያስቀጡ ድንጋጌዎችን የያዘው አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላለፈ።

  • በጨለማ ክፍል የታሰሩ ወጣቶችን የሚያሳይ ሥዕል

    በትግራይ የሚካሄደው የግዳጅ ምልመላ፡ ከክልሉ የሚሸሹ እና ለመደበቅ የተገደዱ ወጣቶች

    በትግራይ እየተካሄደ ያለው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በፈጠረው ስጋት ምክንያት በርካታ ወጣቶች ከክልሉ እየወጡ ወደ ቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል እየሸሹ ሲሆን ሌሎች ደግሞ እዚያው ተደብቀው እንደሚገኙ ተናገሩ። አፈሳው ከነዋሪዎች እና ከመብት ድርጅት ውግዘት እየገጠመው ቢሆንም በፈቃደኝነት የሚካሄድ ነው በማለት ህወሓት አስተባብሏል።

  • በትግራይ የተስፋፋው አፈሳ

    ህወሓት ለግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ያወጣውን ረቂቅ ሕግ "በዝባዥ" በማለት ሂውማን ራይትስ ዋች እንዲሰረዝ አሳሰበ

    የትግራይ ክልል መሪዎች ለወታደራዊ ግዳጅ ምልመላ ለማድረግ "ኃይል የሚሰጣቸውን" እና ተቃዋሚዎችን እንዲቀጡ "መንገድ የሚጠርግላቸውን" ረቂቅ አዋጅ እንዲሰርዙ ሂውማን ራይትስ ዋች አሳሰበ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሰኔ 16/2018 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ህወሓት ረቂቅ አዋጁን ያወጣው በፌደራል መንግሥቱ የተሾሙ የክልሉን አስተዳዳሪዎች ከሥልጣን አውርዶ "ከኤርትራ ብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት ጋር የሚመሳሰል አፈሳ ከጀመረ በኋላ ነው" ብሏል።

  • የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር፣ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አማኑኤል አሰፋ

    አሜሪካ በህወሓት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ማዕቀብ ጣለች

    አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላም በማናጋት ውስጥ ተሳታፊ ናቸው ባለቻቸው አክራሪ የህወሓት አባላት እና የቅርብ የቤተሰብ አባሎቻቸው ላይ የቪዛ ክልከላ መጣሏን አስታወቀች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአክራሪ ህወሓት አባላት እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እንዲያገረሽ የሚያደርግ ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን በመግለጽ ይህም "በቀጣናው ያለውን ሰላም እና መረጋጋት የሚያናጋ ነው" ብሏል።

  • ሰር ኪር ስታርመር በ10 ዓመታት ውስጥ ሥልጣን የለቀቁ ስድስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው

    በ10 ዓመት 6 መሪዎች፡ ለምን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትሮች በቶሎ ይለዋወጣሉ?

    ባለፉት ከ300 ዓመታት በላይ በዩናይትድ ኪንግድም 58 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሥልጣን ይዘዋል። ይህም ዕኩል ቢካፈል ለእያንዳንዳቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሥልጣን ዘመን ይኖራቸዋል። ነገር ግን ባለፉት 10 ዓመታት ስድስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች በሥልጣን ላይ ተፈራርቀዋል። ይህ በአጭር ጊዜ የታየው የበርካታ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለዋወጥ ምክንያቱ ምንድን ነው?

  • የአብን ሊቀ መንበር በለጠ ሞላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የኢዜማ መሪ ኢዮብ መሳፍንት

    አሸናፊው ብልጽግና እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለ ምርጫው ውጤት ምን አሉ?

    የሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ አሸናፊ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ፤ "ዘላቂ ሰላም እና ፀጥታን ለማስፈን" እንዲሁም "የሕግ የበላይነትን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት" በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታወቀ። አብን ባወጣው መግለጫ አሸናፊው ፓርቲ "በሃይማኖት እና በብሔር ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን" እንዲያስቆም ሲያሳስብ፤ ኢዜማ ደግሞ ብልጽግና "ፍትሐዊ የፖለቲካ ምኅዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ" እንዲያደርግ ጠይቋል።

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ

የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት

ከየፈርጁ

ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ

አጃኢብ!

የተመለሱ ጥያቄዎች

የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?

የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!

ሌላ ዕይታ

በስፋት የተነበቡ